ሞዴል የማሕበረሰብ ዓቀፍ ፍትሕ አገልግሎት ማዕከል ሥራዎችን አስመልክቶ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት ተካሄደ

A discussion was held with the business community regarding the activities of the Model Community-Based Justice Service Center

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተቋቋመዉ ሞዴል የማሕበረሰብ ዓቀፍ ፍትሕ አገልግሎት ማዕከል እስካሁን ያከናወናቸዉን ሥራዎችን በተመለከተ እና ማዕከሉን ለነጋዴዉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ያለመ ዉይይት ከክፍለ ከተማዉ ከተዉጣጡ ነጋዴዎች ጋር መስከረም 22/2018 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ተደራሽነትን ለማስፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንሚገኝና ከተግባራቶቹ ዉስጥ የማህበረሰብ አቀፍ ፍትሕ አገልግሎት ማዕከላትን እዉቅና በመስጠት ማስፋፋትና ለመደበኛዉ የፍትሕ ስርዓት አጋዥ እንዲሆኑ ማስቻል አንደኛዉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሞዴል የማሕበረሰብ ዓቀፍ ፍትሕ አገልግሎት ማዕከል ተቋቋሞ ማሕበረሰቡ እየተገለገለበት እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ በተለይም አካባቢዉ የንግድ ማዕከል እደመሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ በዕለት ተዕለት እቅስቃሴዉ ግጭቶች ሲያጋጥሙት ወደ ማዕከሉ በመምጣት ፈጣን፣ወጭ እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በእርቅ፣በድርድርና በሽምግልና ችግሮቹን እንዲፈታ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ከግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዚያቶች ማዕከሉን ከማስተዋወቅ ጀምሮ ሌሎች ለሥራዉ አስፈላጊ የሆኑ ፋይሎችን የማዘጋጀትና የማደራጀት ሥራ ሲሰራ መቆየቱ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን ባለዉ ሂደትም 24 መዛግብት እና በጥቅሉ 102 ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸዉ ተገልፆል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የማሕበረሰብ ዓቀፍ ፍትሕ አገልግሎት ማዕከል በፍትሕ ሚኒስቴር አስተባበሪነት ከኔዘርላንዱ ሄል እና ከደስቲኒ ኢትዮጵያ አገር በቀል አጋር ድርጅቶች ድጋፍ እና ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር በጋራ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በዚሁ ወቅት ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: 2/2018 act activities base based bus business business community center commerce community community-based community-based justice decree Discussion Justice law legislation model proclamation Regulation Service statute un unit unity vice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች