
አቶ መርሻ ብያንሳ ጃተማ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል አቃቤ ህግ ሆኖ እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን የመጀመሪያ ድግሪያቸዉን ከጅማ ዩንቬርሲቲ በ2006 ዓ.ም 2ኛ ድግሪያቸዉን ደግሞ በንግድ ህግ ከአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ በ2015 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ አቶ መርሻ ብየንሳ ተጨማሪ 2ኛ ድግሪያቸዉን በወንጀል ህግ እና ክሪሚኖሎጂ ጨርሶ በአሁኑ ጊዜ የመመረቂያ ጽሁፋ እያዘጋጁ ይገኛል፡፡
አቶ መርሻ ብየንሳ ከ2007 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ ጀማሪ የፌዴራል አቃቤ ህግ በመሆን በፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር አዲስ ከተማ ምድብ ጽ/ቤት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከ2014 ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም ከፍተኛ አቃቤ ህግ በመሆን በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች አቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት አገልግሏል፡፡ አቶ መርሻ ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች አቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክቴር ሆኖ ያገለገሉ ሲሆን ከታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአሁኑ ጊዜ የዳይሬከቶሬቱ ዳይሬክቴር ሆኖ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡