ፍርዴ ቸሩ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ጽ/ቤትን በመምራት ላይ ይገኛሉ።
አሁን ካሉበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ዳይሬክቶሬትን፣ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራልን የመሩ ሲሆን በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተለይም በታክስ እና ጉምሩክ ሥርዓት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች አጥፊዎች በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ በኩል የድርሻቸውን ተወጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በክልል በዳኝነት፣ በሕግና ፍትሕ ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርነት በተለይም በክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊነትና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው በሰሩባቸው የአመራርነት ዓመታት በክልሉ የሕግ የበላይነት እንዲከበርና የፍትሕ ሥርዓቱ እንዲሻሻል በቅንነት እና በእውቀት በመሥራት ውጤት አስመዝግበዋል።
ፍርዴ ሌላውን ልምድ ሳይጨምር በሕግ ሙያ ብቻ ከ23 ዓመታት በላይ ያካበቱትን የሥራ ልምድ እና አመራር ሰጭነት በመጠቀም አሁን እየመሩ ያሉትን የሥራ ክፍል በተገቢው በመነገድ በመምራት የዜጎችን የመሰማት መብት ለመረጋገጥ ዝግጁ ነው።