የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 40 /1/ እና በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6/6/ መሠረት የፌዴራል መንግስቱ ሕጐች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና አተገባበራቸውም ወጥነት ያለው መሆኑን እንዲሁም አስፈፃሚ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ስራዎቻቸውን በሕግ አግባብ ማከናወናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በሕግ ተሰጥቶታል፡፡
በዚህም መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሕግ የተጣለበትን ተግባር እና ኃላፊነት ለመወጣት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በፌዴራል ሕጎች ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ስር የሚያከናውነው የፌዴራል ሕጎች አፈፃፀም ክትትል አንዱ ነዉ፡፡
በቀድሞው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሁኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ውስጥ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008፣የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 568/2000 እና የሀገር ውስጥ አሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ በ2012 ዓ.ም በተደረገው ክትትል መሰረት የአዋጁን አፈጻጸም አስመልክቶ የተስተዋሉ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች የተለዩ ሲሆን ክፍተቶቹ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ምክረ-ሃሳቦች ተሰጥቷል፡፡
እንደሚታወቀው የክትትል ሪፖርቱ ታትሞ ለክትትል ተደራጊ ተቋም እና ለሚመለከታቸው አካላት ተላከ ማለት የክትትል ስራው አበቃ ማለት አይደለም፡፡ ስለሆነም ክትትል የተደረገበት ተቋም በመጀመሪያ የክትትል ሪፖርት መሰረት የተሰጡ ምክረ-ሃሳቦችን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ማድረጉን ለማረጋገጥ፣በሂደት ላይ ያሉ የምክረ-ሃሳቦች የአተገባበር ደረጃዎችን ለመለየት እና በቀጣይነት እንዲተገበሩ ለማድረግ፣ ቀደም ሲል የተስተዋሉ የአፈጻጸም ክፍተቶችን አስመልክቶ በክትትል ተደራጊ ተቋም የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመገምገም እንዲሁም የተሰጡ ምክረ-ሃሳቦችን ለመተግበር ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫን እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማስቀመጥ ዳግም ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በመሆኑም ለዚህ የዳግም ክትትል ምክንያት የሆነው የአፈጻጸም ክትትል ጥናት የተሰራው በቀድሞው የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ቢሆንም፤የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ተሻሽሎ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 25 ስር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰሪና ሰራተኛን በሚመለከት ተሰጥቶ የነበረው ተግባር እና ኃላፊነት ለስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘዋወረ በመሆኑ ከላይ የተገለጹት አዋጆች አፈጻጸም አስመልከቶ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ላይ ዳግም ክትትል ተከናውኗል፡፡
ይህ የምክረ ሀሳብ ክትትል ዓላማ በቀድሞ ክትትል የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው ወይም አለመደረጋቸው እንዲሁም የአተገበባር ሁኔታቸው ያለበትን ደረጃ ለመለየት ነው። በሌላ በኩል ተግባራዊ ያልተደረጉ ምክረሃሳቦች ካሉ ምክንያታቸውንና በዚህ ረገድ ተቋሙ የወሰደውን አቋም ወይም እርምጃ ለማየት ነው።
የተሰጡ ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው ወይም አለመደረጋቸው እንደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አግባብበነትና ተቀባነይነት ያለው መረጃ ሊሰጥ ከሚችል አካል ጋር የበላይ ኃላፊን ጭምር ያካተተ በተሰጡ እያንዳንዱ ምክረ ሀሳብ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በዚህም መሠረት በሕግ ክትትሉ ከተሰጡት ምክረ ሃሳቦች ጋር በተያያዘ ቁልፍ መረጃ የሚገኝባቸውን የስራ ክፍሎች ማለትም የብቃት እና የሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ፣የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት መሪ ስራ አስፈጻሚ (MIS)፣የሕግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ፣የስነ-ምግባር ስራ አስፈጻሚ፣ የስራ ስምሪትና ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ፣የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ፣የሰራተኛ ስምሪት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣የስራ ዕድል ፈጠራ ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ፣የፖሊሲ እና እስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ፣የሪፎርም እና ተቋማዊ አደረጃጀት ስራ አስፈጻሚ፣የሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ስራ አስፈጻሚ ጋራ በተገኙበት መድረክ ላይ በምክረ ሀሳቦች አተገባበር ላይ ተቋሙን በመወከል የሰጡት ሀሳብና አስተያየት እንደተቋሙ ሀሳብ ተወስዷል። እንዲሁም ክትትሉ ከተደረገ ወዲህ በተሰጠው ምክረ ሀሳብ መሰረት ይሁን በሌላ ምክንያት የተከናወኑ የሕግ እና የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች የሚያሳዩ የሰነድ ማስረጃዎች በአስረጂነት እንዲቀርቡ ተደርጓል።
የዚህ የምክረ ሀሳብ ክትትል ሪፖርት እንደሚከተለው በሰንጠረዥ ቀርቧል። ሰንጠረዡም የተሰጡ መክረ ሀሳቦች ዝርዝር፣ የምክረ ሀሳቦች አተገባበር ሁኔታ ማለትም ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የተደረጉ፣ በከፊል ተግባራዊ ተደረጉ እና ምንም ተግባራዊ ያልተደረጉ ምክረ
ሀሳቦችና ያካተተ መረጃ እንዲይዝ ተደርጓል። በመጨረሻም ሪፖርቱ ማጠቃለያ ሃሳብ እንዲኖረው ተደርጓል።