ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን የማበረታታት ሚና ያለው፤ የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በዕቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከወጣ ወዲህ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ረገድ የተደረጉ ለውጦችን በተለይም የኤሌክትሮኒክ ግብይትን እና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት ያገኙ አዳዲስ እሳቤዎችን በሀገራችን የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት ታክሱ ለኢኮኖሚው ዕድገት የሚፈለገውን እገዛ እንዲያደርግ ማስቻል ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤
መሰረታዊ የሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ድንጋጌዎችን በአዋጁ ውስጥ በማካተት እና ዝርዝር ድንጋጌዎችን ለደንብና መመሪያ በመተው አዋጁ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል አወቃቀር እንዲኖረው እንዲሁም ለአፈጻጸም ግልጽ እና ምቹ እንዲሆን ማድረግ በሚያስችል አኳኋን መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ከታክሱ ነጻ የመሆን መብት አተገባበር የመብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የታሰበውን የህብረተሰብ ክፍል ማእከል ያደረገ እና በግብአት ታክስና በውጤት ታክስ መካከል ያለውን ሰንሰለት የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ ፍትሐዊነትንና የዜጎችንም ሆነ የንግድ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 99 መሠረት ሚያዝያ 3 ቀን 1994 ዓ.ም በተካሄደው የፌደሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ የጋራ ስብሰባ እና በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት በተሰጠ ሥልጣን የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•