በአገልግሎት ላይ

የከተማ ፕላን አዋጅ

የተመጣጠነና የተቀናጀ ብሔራዊ፣ ክልላዊና አካባቢያዊ ዕድገትን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ፕላን ሳይኖራቸው ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡ ከተሞችን ትክክለኛና ራዕይ ባለው የከተማ ፕላን መምራትና መቆጣጠር በማስፈለጉ፤

የመንግሥትም ሆኑ የግል ያገባኛል ባዮች አገር አቀፍ መስፈርቶችን በጠበቀ አኳኋን የከተማ ፕላን ሃሣብ ማመንጨትን፣ አዘገጃጀትንና አፈፃፀምን አስመልክቶ በሚደረገው የአሠራር ሂደት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በማስፈለጉ፤

በግልም ሆነ በመንግሥት አካላት የሚከናወኑ የልማት ተግባራት የጠቅላላውን ሕብረተሰብ ጤንነትና የተፈጥሮ አካባቢን ደህንነት በማይጐዳ መንገድ እንዲሁም ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ መከናወናቸውን መቆጣጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በሥራ ላይ ያሉት የከተማ ፕላን ሕግጋት አሃዳዊ በሆነ የመንግሥት ሥርዓት የወጡና አሁን ካለው ያልተማከለ አሰራር መንፈስ ጋር የማይጣጣሙ ከመሆናቸው የተነሳ ፌደራላዊውን የመንግሥት አወቃቀርና በከተማ ፕላን ዝግጅትም ሆነ ተፈፃሚነት ረገድ ከተሞች ሊኖራቸው የሚገባውን በሚያመለክት ሁሉን አቀፍ ሕግ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 574/2000
ቀን: ግንቦት 8፥ 2000 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ