የተሻሻለ

የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ

የድሬዳዋ ከተማ የሱማሌና የኦሮሚያ ክልሎች ወደየክልላ ቸው ይዞታ እንዲካለል በወቅቱ አንስተውት የነበረው ጥያቄ በህግ መሠረት የመጨረሻ ውሣኔ እስኪያገኝ በመንግስት በተወሰነው መሠረት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ ሆኖ ሲተዳደር የቆየ ከተማ በመሆኑ፤

ዘላቂ የሆነ ህጋዊ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ የድሬዳዋ ከተማ ለጊዜው እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ህጋዊ መሠረት መጣል ለከተማው መልካም አስተዳደርና ልማት መፋጠን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ከተማው ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የንግድ፣ የኢንዱ ስትሪና ሌሎች አገልግሉቶች ለመስጠት አቅም እንዲኖረው ለማስቻል ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ፣

ድሬዳዋ የነዋሪዎቹ ሁለንተናዊ ብልጽግና የተጠበቀበት ዘመናዊና ተወዳዳሪ የሥራና የመኖሪያ፣ ቀልጣፋና አዋጭ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት በፍትሀዊነት የሚሰጥበት ከተማ ሆኖ የሚተዳደርበትን ሁኔታ በግልጽ መደንገግ በማስፈለጉ፤

ለድሬዳዋ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሥልጣን መስጠትና የከተማውን አስተዳደር አደረጃጃትና አሠራር ከዲሞክራሲ መርሆዎችና ከመልካም የአስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም ከወቅታዊ የዕድገት የልማት አቅጣጫ ጋር በሚጣጣም መልኩ በህግ መወሰን በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 416/1996
ቀን: ሐምሌ 23፥ 1996 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

590/2018

•

ግንቦት 10÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
586/2018

•

የካቲት 16÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
586/2018

•

የካቲት 16÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ