የተሻረ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማደስ የወጣ አዋጅ

የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 1/2000 መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምከር ቤት ታውጆ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 984/2009 ከፀደቀ በኋላ በሕገ መንግስቱና በሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የተቃጣውን አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል ባለፉት ስድስት ወራት በተሰራው ስራ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ማድረስ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እንዲሁም ህብረተሰቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚነቱ እንዲቀጥል ያለውን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 93(3) እና አንቀፅ 55(5) መሠረት የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለቀጣይ አራት ወራት እንደሚከተለው ታድሷል:-

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1004/2009
ቀን: ሚያዚያ 11፥ 2009 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1083/2010

መጋቢት 14፥ 2010 ዓ.ም.
የተሻረ