በባንኮች በዋስትና የተያዙ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲሸጡ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰንና ውሳኔውንም ለማስፈጸም የሚወስደው ጊዜ በጣም ረጅም በመሆኑ፤
በቁጠባ ሂሣብ መልክ ከሕዝብ የሰበሰቡትንና ከተለያዩ ምንጮች ያገኙትን ገንዘብ በማበደር በሚገኘው የወለድ ገቢ የሚተዳደሩ ባንኮች ሥራ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደሩ፤
ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴው አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ባንኮች ለተለያዩ የንግድና የልማት እንቅስቃሴ የሚሰጧቸው ብድሮችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመሰብሰብ እንዲችሉና ለወደፊቱ ጥሩ የንግድ አሰራር ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ለባንክ ብድር በመያዣ የተሰጡ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሽያጭ በሚመለከት በሥራ ላይ ያሉትን ሕጎች ማሻሻልና አዲስ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•