የትራንስፖርት አገለግሎት የአገራችንን ልማት ለማሳካት፣ ለአጠቃላይ የንግዱ ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለሕዝቦች መቀራረብ ውሳኝ ሚና የሚጫወት የአገልግሎት ዘርፍ በመሆኑ፤
በማናቸውም የማጓጓዣ ዓይነት ዕቃ ማጓጓዝን የሚመለከቱ የአገራችን የትራንስፖርት ሕጐች አንዱ ከሌላው ጋር መጣጣምና ተቀናጅቶ አገልግሎት በመስጠት ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ መወጣት የሚጠበቅበት በመሆኑ፤
ከዚህ አንፃር በ1952 ዓ.ም በንግድ አማካኝነት ወጥቶ በሥራ ላይ ያለውን ሕግ በተለይም የአጓጓዦችን የኃላፊነት መሠረት፣ የኃላፊነት መጠን ወሰንና ሌሎች መብቶችና ግዴታዎችን አስመልክቶ ዓለም ዓቀፍ ይዘት ካለውና በአዋጅ ከወጣው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አሠራር ጋር በማቀናጀት ወጥ የሆነና የተቀላጠፈ አግልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ አሻሽሎ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•