በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት የደህንነት ስጋት ብቻም ሳይሆን የፋይናንስ ሥርዓቱ የተረጋጋ፣ ግልጽነት ያለው ጤናማና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ በመሆኑ፤
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመወጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረት እየተደረገ በመሆኑ እና ኢትዮጵያም የዚህ ዓለም አቀፍ ጥረት አካል በመሆኗ፤
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን በሚመለከት በወንጀል ሕግ የተደነገገውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም የሚያስችል የተለየ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡