በአገልግሎት ላይ

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት የደህንነት ስጋት ብቻም ሳይሆን የፋይናንስ ሥርዓቱ የተረጋጋ፣ ግልጽነት ያለው፣ ጤናማና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ በመሆኑ፤

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመዋጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረት እየተደረገ በመሆኑ እና ኢትዮጵያም የዚህ ዓለም አቀፍ ጥረት አካል በመሆኗ፤

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 780/2005
ቀን: ጥር 26፥ 2005 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 171/2002

•

የካቲት 5፥ 2002 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ