ዜጎች በየደረጃው በሚካሄድ ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫ በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሥልጣናቸውን በተግባር እንዲያውሉ ለማድረግ ነፃ የምርጫ አስፈፃሚ አካል አስፈላጊ በመሆኑ፣
በኢትዮዽያ ዲሞክራሲን ለማጠናከር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን : ከማንኛውም አካል ነፃ አድርጎ በማደራጀት ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈፀም የሚያስችለው መዋቅር እንዲኖረው
ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን አመላመልና አሿሿም አሳታፊና ግልጽ በማድረግና የቦርዱን የመዋቅር፣ የሰራተኛ ቅጥርና ምደባ እንዲሁም የበጀት ነፃነት በማረጋገጥ በተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችና በመራጩ ዘንድ ያለውን ተዓማኒነትና የማስፈፀም አቅሙን ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (102) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•