ለሴቶች የንግድ ስራ ፈጠራ ብቃት ማሳደጊያ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 5 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን የጃፓን የን (አምስት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን የጃፓን የን) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በጃፓን ዓለም ዐቀፍ የትብብር ድርጅት መካከል የካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፤-
•