ለሁለተኛው አሳታፊ አነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 71 ሚሊዮን 950 ሺ ኤስ.ዲ.አር (ሰባ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ ግብርና ልማት ፈንድ መካከል ሕዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በሮም የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦