ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 70 ሚሊዮን 900 ሺህ ኤስ.ዲ. አር (ሰባ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ኤ ስ.ዲ.አር) ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር መካከል ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 10 ኛ መደበኛ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•