በአገልግሎት ላይ

የሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለሴቶች ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ ኤስዲ አር 3 ሚሊዮን 800ሺህ (ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺ ኤስዲ አር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ኦገስት 28 ቀን 2ሺ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፡

መሠረታዊ የኤኮኖሚ ዓለምአቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፡

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 22 ቀን 1993 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 231/1993
ቀን: ጥር 22፥ 1993 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች