ለርቀት ትምህርት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 3 ሚሊዮን 900ሺ ኤስዲ‧አር (ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ኤስዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ሜይ 1 ቀን 2ሺ 1 በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መፅደቅ ስላለባቸው ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 21 ቀን 1993 ዓም· ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•