ሕጎችን ከወቅታዊ የአገሪቱ የእድገት ደረጃና የልማት ፍላጎት ጋር በማጣጣም እና የፍትህ ሥርዓቱን ዘመናዊ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስትን በተሟላ ሁኔታ ስራ ላይ ለማዋል፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዲሞክራሲያዊና ልማታዊ የእድገት አቅጣጫን መሰረት ያደረገ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን እውን ለማድረግ የሚረዱ የፍትህና የሕግ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የአገሪቱ የፍትህ ሥርዓት የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እያሳካ መሆኑን የሚያሳይ አስተማማኝና የተሟላ መረጃ መኖር ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ለሚከናወኑ ሥራዎች በግብዓትነት የሚያገለግል መሆኑን በመገንዘብ፤
በእውቀቱ፣ በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ፣ እንዲሁም በሥነ ምግባሩ ብቁ የሆነና የተሟላ ስብዕና ያለው አመራር እና ባለሙያ ለማፍራት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን በመስጠት የፍትህ ዘርፉን የማስፈጸም አቅም ማሳደግ በማስፈለጉ፤
በፍትህ ሥርዓቱና በሕግ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረጉ የማሻሻያ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመምራትና ለማስፈጸም የሚያስችል አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በተለያዩ ተቋማት በተበታተነ ሁኔታ ይሰሩ የነበሩ የሕግ ጥናትና ምርምር፣ አቅም ግንባታና፣ የፍትህ ማሻሻያ ተግባራትን በማጠቃለል በአንድ ተቋም እንዲከናወኑ ማድረግም ሆነ በተቋማቱ መካከል ያለውን የኃላፊነት ድግግሞሽ ማስቀረት ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ በመገንዘብ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•