የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፖለቲካ ሥልጣን ባለቤትነት እንዲሁም ለሕግ ልዕልና እውነት ባካሄደው ረጅም ትግል የከፈለው መስዋዕ ትነት በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቀበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት ለሰናይ መስተዳድር መሠረት የመጣልን ወቅታዊ እርምጃ የሚጠይቅ በመሆኑ፤
የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚያከናውኗቸው ተግባሮች ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር ያላቸው ቁርኝትና ከመብታቸው ጋር በተሳሰረ ሁኔታ የሚኖራቸው የወሳኝነት ሥልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየሰፋ በመምጣቱ፤
በዚህ ሂደት የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ባለሥልጣኖቻቸው የሚሰጧቸውን ፍትሃዊነት የጎደላቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች በወቅቱ ማረም ወይም እንዳይደርሱ መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፤
አስተዳደራዊ ጥፋት የተፈጸመባቸው ዜጎች ተጎድተው እንዳይቀሩ በቀላሉ ቅሬታቸውን የሚያሰሙበትና መፍትሄ የሚሹበት ተቋም የማግኘት ፍላጎታቸው መሟላት ያለበት በመሆኑ፤
ሕግ አውጪው በሕዝብ ተወካይነቱ ሕግ አስፈጻሚው አካል ተግባሩን በሕግ መሠረት የሚያከናውንና የሚሰጣቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የዜጎችን መብቶች የማይጋፉ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፤
ይህንኑ መርህ ለማጎልበትና ስለሕግ አውጪው ሆኖ አስተዳደራዊ በደል እንዳይደርስ የመቆጣጠሪያ መሣሪያ በመሆን ከሚያገለግሉት ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነውን የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ማቋቋምና ሥልጣኑንና ተግባሩን በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (15) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•