ለስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 91 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (ዘጠና አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በሕንድ የኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 18 ቀን 2011 በኒውዴልሂ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 11 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሔደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•