በአገልግሎት ላይ

በግል ክፍለ ኢኮኖሚ ለተሠማሩት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካይነት በመልሶ ማበደር የሚተላለፉ ከአዉሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

በግል ክፍለ ኢኮኖሚ በፋብሪካ፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በመሳሰሉት የሥራ እንቅስቃሴዎች ለተሠማሩት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካይነት በመልሶ ማበደር የሚተላለፍ መጠኑ 10 ሚሊዮን (አሥር ሚሊዮን) ኢኪው የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክ ራሲያዊ ሪፐብሊክና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ ዲሴምበር 18 ቀን 1996 በሉግዘምበርግ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 17 ቀን 1989 ዓ·ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 85/1989
ቀን: ሰኔ 26፥ 1989 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች