ለከተሞች ማከፋፈያ መስመር እና የኃይል ሥርጭት መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ዩሮ 25,000,000 (ሃያ አምስት ሚሊዮን ዩሮ) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል እኤአ ዲሴምበር 9 ቀን 2002 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 29ቀን 1995 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12)መሠረት የሚከተለው ታውጇል።