ለኢትዮጵያ ቀጣይ የኢኮኖሚ እድገት የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማ፣ ለአደጋ ያልተጋለጠና የተረጋጋ በማድረግ ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፤
የገንዘብ አስቀማጮች ጥበቃ ለፋይናንስ ሥርዓት መረጋጋት አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፤
የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ እንደ አንድ ተጨማሪ የሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ማረጋጊያ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤
በመድን ክስተት ወቅት በመድን የተሸፈነ ተቀማጭ ገንዘብ ላለዉ አባል የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ አስቀማጮች ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ፈንድ ማቋቋምና ማስተዳደር አስፈላጊ በመሆኑ፤
ከብሔራዊ ባንክ፣ ከአባል ፋይናንስ ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመሥራት ተጋላጭነትን መቀነስና ለፋይናንስ ሥርዓቱ መረጋጋት አስተዋጽኦ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2ሺ (እንደተሻሻለ) አንቀጽ /25/ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡
•
•
•
•
•
•
•