በሀገራችን በሕገ መንግስቱና በሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ላይ ተጋርጦ የነበረው አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል በማሳየቱ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ የተደረሰ በመሆኑ ሕገ- መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሻር አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
አሁን የታየውን አንፃራዊ ሠላም በመንግስትና በሀገራችን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀጥተኛ ተሳትፎ እና ባለቤትነት በማረጋገጥ የተጀመረውን ልማትና ዴሞክራሲ ማስቀጠል አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራሊዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት ይህን አዋጅ አውጥቷል::