የማይንቀሳቀስ ንብረትን በመያዣነት ለመስጠት ስለ ሚደረግ ውል በፍትሐብሔር ሕግ የተደነገገው ሥርዓት የባንኮችና የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ዋነኛ የዕለት ተዕለት ተግባር በሆነው የብድር አቅርቦት አገለግሎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ሆኖ በመገኘቱ፤
ባንኮችና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ሲከተሉት በቆየው አሠራር መሠረት ያደረጓቸው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውሎች በፍትሐብሔር ሕጉ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት ሥልጣን ባለው አዋዋይ ፊት የተፈረሙ ባለመሆናቸው እንዲፈርሱ ቢደረግ የሰጧቸውን ብድሮች በአብዛኛው ዋስትና የለሽ በማድረግ በባንኮቹና በአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማቱ ህልውናና በጠቅላላው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብ ሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•