በአገልግሎት ላይ

ለብሔራዊ የማዳበሪያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር ብድር ለማግኘት የተፈረመውን የብድር (ማሻሻያ) ስምምነት ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ

ለብሔራዊ የማዳበሪያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ኤስዲ አር 82 ሚሊዮን 900 ሺ (ሰማንያ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺ ኤስዲ አር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ሴፕቴምበር 29 ቀን 1995 የተፈረመ በመሆኑ፣

ለፕሮጀክቱ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ ኤስዲ አር 34 ሚሊዮን 700 ሺ (ሠላሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺ ኤስዲ አር) ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር በብድር ለማግኘት የሚያስችል የማሻሻያ ስምምነት እኤአ ጁላይ 18 ቀን 2001 በዋሽንግተን ዲሲ ስለተፈረመ ፡
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆ ናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው፣

ይህንኑ የማሻሻያ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 1993 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 252/1993
ቀን: ሰኔ 29፥ 1993 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች