የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ የወጣቶች ቻርተርን እ.አ.አ. ጁላይ 2 ቀን 2006 ዓ.ም በባንጁል ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ያወጣ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ቻርተሩን እ.አ.አ ዲሴምበር 28 ቀን 2007 ዓ.ም የፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ቻርተር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡