የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በሀገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውና እ.ኤ.አ ሰኔ 27 ቀን 1993 የወጣው የማድሪድ ፕሮቶኮል ማጸደቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ፕሮቶኮሉ ለአባል ሀገራት ለንግድ ምልክት ጥበቃ ተገቢውን ዋስትና የሚሰጥ በመሆኑ እና በሀገራችን ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እና ቴክኖሎጂዎች እንዳይገቡ የሚያደርግ በመሆኑ፤
የፕሮቶኮሉ አባል መሆን የእደ-ጥበብ ምርቶቻችንን የንግድ ምልክቶች በማስጠበቅ አምራቾች እንዲሁም አገልግሎት ሰጭዎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያግዝ በመሆኑ፤
የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀልጣፋ፣ ጊዜንና ወጭን ቆጣቢ በሆነ መንገድ መመዝገብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
ይህንኑ ስምምነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 4 መደበኛ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•