የግልግል ዳኝነትና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት መዘርጋቱ የአለመግባባት መፍቻ አማራጮችን በማስፋት ፍትሕ የማግኘት መብትን ለማሟላት አጋዥ በመሆኑና በተለይም የኢንቨስትመንትና ንግድ ነክ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ለዘርፉ እድገት አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ፤
የግልግል ዳኝነት እና ዕርቅ የተዋዋይ ወገኖችን ወጪ በመቀነስ፣ ምስጢርን በመጠበቅና ልዩ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች በዳኝነት እንዲሳተፉ በማድረግ እንዲሁም ቀላልና ለተዋዋይ ወገኖች ነፃነት ያለው ሥነ ሥርዓት ለመጠቀም በመፍቀድ የተቀላጠፈ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል በመሆኑ፤
የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በግልግል ዳኝነት የሚታዩ ጉዳዮችን ለመለየት፣ ሂደቱ የሚመራበትን እና ውሳኔ የሚፈጸምበትን አጠቃላይ ማዕቀፍ መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ አጋዥ በመሆኑ፤
ከግልግል ዳኝነትና ከዕርቅ ጋር በተያያዘ የዳበሩ ዓለም አቀፍ አሠራሮችንና መርሆችን ታሳቢ በማድረግ በሥራ ላይ ያሉ ሕጎችን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡