የመመሪያ መለያ: 708/2013
ቀን: ሰኔ 27፥ 2004 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሥራ ቦታ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መመሪያ ቁጥር 708/2013

የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት የዓለማችን ከፍተኛ ችግር ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ እያስከተለ ያለው ችግርም : ከጤና ችግር በላይ በመሆን የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ቀውሶችን አስከትሏል፣ በማስከተል ላይም ይገኛል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት፣ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት እየተፈታተነም ነው፡፡ ቫይረሱ እያስከተለ ያለው ሰብዓዊ ጉዳት አስከፊ ከመሆኑም በተጨማሪ መ/ቤቶች የሰለጠነ ባለሙያ እንዲያጡ፣ ሥራ ያልተሰራባቸው መደበኛ የሥራ ቀናት እንዲበዙ፣ ተተኪ የሰው ኃይል ለማሰልጠን የሚያስፈልግ ተጨማሪ ወጪ እንዲያድግ፤ የተቋማት የሕክምና፣ የካሣ ክፍያና የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ እንዲንር፣ በአጠቃላይ የተቋማት የሥራ ውጤትና ትርፋማነት እያሽቆለቆለ እንዲሄድ ተፅዕኖ በማድረግ በሀገሪቱ አጠቃላይ ልማትና እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

መንግሥት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታትና እያስከተለ ያለውን ፈርጀ ብዙ ጉዳት ለመቀነስ በተቀናጀ ሁኔታ ለመቆጣጠርና ለመከላከል ይቻል ዘንድ ብሔራዊ ፖሊሲ በማውጣት እና ይህንንም ፖሊሲ መሠረት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡንና የልማት አጋሮችን ያሳተፉ በርካታ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እነዚህን ጥረቶች ይበልጥ አጠናክሮ ውጤታማ ለመሆን፣ በሥራ ቦታዎች የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ወጥነት ያላቸውና በሀገራዊው የጤና ፖሊሲ መርሆዎች ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ በተደረገው እንቅስቃሴ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በሴክተሮችና በተቋማት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መመሪያዎች በመቅረጽ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም ይህንኑ ሁኔታ አጠናክሮ በመቀጠል ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት ለመስጠትና የኤድስ ህመምተኛ ለሆኑት ደግሞ አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ ለማድረግ፣ በሀገራዊው የጤና ፖሊሲ መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የሥራ ቦታ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መመሪያ አዘጋጅቷል ::

ይህ መመሪያ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የመንግሥት መ/ቤቶች የስራ ቦታዎች ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲችሉ በወጣዉ መመሪያ አራት ተራ ቁጥር 4.1 መሠረት ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration