የመመሪያ መለያ: 109/2014
ቀን: ጥር 18፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመሥሪያ ቦታ አሰጣጥ፣ አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 109/2014

የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ኢንዱስትሪ ልማት ለአገርኢኮኖሚ እድገት እና ሥራ አጥነትን በመቀነስ ረገድ ያላቸው አስተዋጾ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ እንደ አገራችን በማደግ ላይ ላሉ አገሮች እነዚህን ኢንተርፕራይዞችንና ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እርስ በእርሳቸው የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የግብዓት ትስስርእንዲያደርጉ፣ ከከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችም ጋር የምርት ቅብብሎሽ ትስስር በመፍጠርና ኤክስፖርትንና ገቢ ምርት መተካትን ታሳቢ ያደረጉ ምርቶችን ለገበያው በስፋት ማቅረብ እንዲችሉ በማድረግ አገራዊ የኢኮኖሚ ልማት አስተዋጾቸውን እንዲያጎልብቱ በማድረግ የአገራችን ትልቁ ችግር የሆነዉን ድህነትና ሥራ አጥነትን በመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ይህን አስተዋጽኦ እውን ለማድረግ የተለያዩ የድጋፍ ፖኬጆች ተዘጋጅተው ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ከድጋፎቹ አንዱ መሰረተ-ልማት የተሟላላቸው መስሪያ ቦታዎችን በኢንዱስትሪ መንደሮች፣ በክላስተር ማዕከላት፣ በገበያ ማዕከላት እና በኢንፓሪየም ማዕከላት አደራጅቶ በማስገንባት የማምረቻና የመሸጫ ቦታ አቅርቦት ነው። የመስሪያ ቦታ ድጋፍ ሲደረግ ቀጣይነት ያለው ምርታማነትና ውጤታማነት እንዲሁም ተወዳዳሪነትን በሚያረጋግጥ አኳሃን በግልፅ አሠራር እና ተጠያቂነት ባለው መንገድ ያለን ውስን ሃብት ፍትሃዊና ብክነት የቀነሰ በሆነ አግባብ ማስተላለፍና ማስተዳደር እንዲሁም በማዕከል፣ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ባለው የቢሮው መዋቅር ተጠያቂነት ያለበት የሥልጣን ወሰን ማስቀመጥ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት በተለያዩ ተቋማት ሲተዳደርየነበረው መስሪያ ቦታ ወደ አንድ ለማምጣት እና የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 እና አንቀጽ (3) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration