የመመሪያ መለያ: 364/2013
ቀን: ኅዳር 1፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የስራ ልብስና የስራ መሣሪያ አፈቃቀድና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 364/2013

የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት አጠባበቅ ከሥራ ጋር የተያያዙ የጤንነትና የደኅንነት አጠባበቅ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን፣ ዓላማውም የሠራተኞችን ደኅንነትና ጤንነት መጠባበቅ፣ የሥራ ብቃት ማጎልበት፣

የሥራ ቦታን ለሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት በሚስማማ መልኩ ማዘጋጀት፣ ማደራጀት ማሻሻልና መጠበቅ እንዲሁም መሥሪያ ቤቱ በጎ በሆነ ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ተመስርቶ አመርቂ የሥራ ውጤት እንዲያስመዘግብ ማብቃት ነው፡፡

የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት አጠባበቅ በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 48/ለ ላይ “በማናኛውም መንግሥት መሥሪያ በብት የአደጋ መከላከያና ቁሳቁሶችን ለሠራተኞች የማቅረብና ስለአጠቃቀማቸው መመሪያ የመስጠት ኃላፊነት አለበት” በሚል ተደንግጓል፡፡

ስለዚህም በኢንስቲትቱ ደረጃ የሚያስፈልገውን የተጠቃለለ መመሪያ ለማዘጋጀት ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ጥናት የሚችሉትን ለብቻቸው አጥንቶ በማስፀደቅ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ በኢንስቲትታችን የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ባለሙያ ተጠንቶና የደንብ ልብስ ተጠቃሚዎች አስተያት እንዲሰጡበት ተደርጎ የታመነባቸው ነጥቦች ከተካተቱ በኋላ ይህን የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችና የደንብ ልብስ ጥናት አፈጻፀም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Ethiopian Public Health Institute

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration