የመመሪያ መለያ: 649/2013
ቀን: ሰኔ 1፥ 2007 ዓ.ም.
Language: Amharic

የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች የሙያ ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 649/2013

ሙስና ባደጉም ባላደጉም አገሮች ተንሠራፍቶ የሚገኝ ጸረ-እድገትና ሰላም ነው፡፡ ሙስና በአንድ አገር ውስጥ የሚገኙ ማናቸውም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጉዳ ችግር ነው፡፡ ያደጉ አገሮች (Developed Countries) የከፋ ችግር ሣያስከትል መቆጣጠር ቢችሉም በማደግ ላይ ያሉ ድሀ አገሮች ግን ህልውናቸውም ጭምር እየተፈታተነ ይገኛል፡፡ ሙስና በመንግሥት ተቋማት ብቻ ሣይወሰን በግል ተቋማትም ተንሰራፍቶ የሚገኝ የሀብት ክፍፍልን በእጅጉ የሚጉዳ፣ የእኩልነት መርህን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የዘመኑ በሽታ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሣዩት ሙስና በመንግሥት የፖለቲካ ሹመኞች፣ በሀኪሞች፣ በግሙሩክ ሠራተኞች፣ በመንግሥት ካምፖኒ ማናጀሮች፣ በፖሊስ፣ በግል ድርጅት ባለሀብቶች፣ በከተማ ማዘጋጀ ቤት ሠራተኞች፣ በዳኞች፣ በአስተማሪዎች፣ በተለያዩ ማህበራት አመራሮች …ወዘተ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተፈፀመ ያለ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ሽፋን ያለው ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች ከሙያ ስነ-ምግባር ባህርይ ውጭ (Non-ethical behavior) ከሁኑት እንዱ የሆነው ለሙስና ሊጋለጡ ይችላሉ ወይ ብለን ሲንጠየቅ አዎ የሚል መልስ እናገኛለን፡፡ የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች ዋና ተግባራቸው አግባብ ያላቸው አሠሪና ሠራተኛን የተመለከቱ ህጐች (በሙያ ደኅንነትና ጤንነት እንዲሁም የመሠረታዊ የስራ ሁኔታዎች) በስራ ላይ መዋላቸውን የማረጋገጥና የመቆጣጠር ነው፡፡ ይህንን ሰፊ ተግባር ሲያከናውኑ በተለይ በአሠሪ ላይ የተለያዩ አስገዳጅ ትዕዛዞችን (Notices) እና ውሳኔዎች የማስተላለፍና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ አጥፊውን የማስቀጣት ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በተጨማሪም በድርጅቶች ቁጥጥር ሲያከናውኑ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የድርጅት ሰነዶችን የማየትና የመቅዳት ፣ ፎቶ ግራፍ የማንሣት ፣ አሠሪዎችና ሠራተኞች በግል ወይም በጋራ የማነጋገር…ወዘተ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

በዚህም መሠረት የድርጅቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪ እጅ ይገባሉ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው አሰሪዎች ከሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች የሚተላለፉ መመርያዎች ለመፈጸም ወይም ለሟሟላት የግድ ወጪ ማውጣት ስለማይቀርባቸው ወጪያቸውን ለመቀነስ እንዲሁም ከቅጣት ለመዳን የተወሰኑ አሰሪዎች የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎችን በጥቅም ሊደልሉ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል በአሁኑ ሰዓት መረጃ ማለት ትልቅ ሀብት ነው:: አንድ ካምፓኒ ወይም ድርጅት ሌላኛውን ጥሉ ለማለፍ የካምፖኒውን ሚስጢራዊ መረጃ እንደምንም ብሎ በማግኘት ለዚሁ ዓላማ ለማዋል መፈለጉ አይቀርም፡፡ ይህንን መረጃ ከየ አገኘዋለሁ ብሎ ሲያስብ ደግሞ የመረጃው ምንጭ ሊሆኑ ከሚችሉ አንዱ የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን የመረጃ ፍላጉቱ ለሟሟላት ከስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎቹ አሁንም በድጋሚ በጥቅም መደራደር ሊኖር ይችላል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች ፍላጎቶች (Conflict of interest) ለማሰጠበቅ በአሠሪና በስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪ መካከል በሚከተሉት መንገዶች ሙስና ሊፈጸሙ ይችላሉ፡፡

  • አሠሪው እንዳይከሰስ፣ እንዳይቀጣ ወጬዎችን እንዳያወጣ በቀጥታለስራ ሁኔታተቆጣጣሪውገንዘብ በመስጠት፣ የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪው ወደ ስራ ቦታ ለቁጥጥር ስሄድ ድርጅቱ ከማያሚታቸውነ ገ ሮች በነ ጻ እንዲወስድ በማድረግ፣
  • የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪው ከአሠሪው በብድር ቁስ ነገር ወይም ጥሬ-ገንዘብ እንዲወስድ ማድረግና በኋላ ግን ብድሩን እንዳይከፍል ሁኔታዎች በማመቻቸት፣
  • የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪና ሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ ፍትሓዊ ያልሆኑ እና ጎጂ መያዎች እንዲያስተላልፍ በጥቅማጥቅሞች መደለልን የመሳሰሉትን ይገኙበታል፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሙያን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊቶች በአገልግሎት አሠጣጡና በአጠቃላይ በማህበረሰቡ የሚያስከትሉት ተጽእኖዎች እጅግ ከባድ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሰጠው ተግባርና ሓላፊነት መሠረት ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ተአማኒነት፣ ታማኝነት፣ ፍትሓዊነት፣ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ይችል ዘንድ ይህንን የስራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎች የሙያ ስነ-ምግባር መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

Ministry of Labor and Social Affairs

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration