በኢትዮጵያ መንግሥትና _ በዓለም ባንክ መካከል በተደረሰ ስምምነት መሠረት የሴቶችን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማትፕሮጀክት (Women Entrepreneurship Development Project) ተዘጋጅቶ ከባንኩ ጋር የ50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በመሆኑም የፕሮጀክቱ የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎችን በማጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ባለቤት በሆነው በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና ሚኒስቴር መ/ቤቱን ወክሎ ፕሮጀክቱን በሚያስፈጽመው የፌደራል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ከአሰፈጻሚ መ/ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
ከዚህ አንጻር የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማስፈፀምና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፀደቀው የፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ሠነድ መሠረት ስራውን የፌዴራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ካውንስል የሚከታተለው ሲሆን የሚኒስቴር መ/ቤቱም ከፕሮጀክቱ ፈጻሚ መ/ቤቶች ጋር አብሮ ለመሥራትና ለማስተባበር የተደረጉ ጥረቶችን ማጠናከር አስፈልጓል፡፡
ይህም በመሆኑ ፕሮጀክቱ ለተጠቃሚዎቹ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግና የታለመለትን ዓላማ ማሳካት እንዲቻል በእድገት ተኮር የስራ ዘርፎች የተሰማሩትን ሴት ኢንተርፕረነሮች ገቢ ማሳደግና ስራ ፈጣሪ ለማድረግ የሚያስችሉ የቴክኒዮሎጂ የፋይናንስና የገበያ እንዲሁም የመስሪያ ቦታ አቅርቦት አስፈላጊ ይሆናል፡፡
አቅርቦቶችን ከማጠናከርና ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር በተለይ በምርት ተግባር ላይ (Manufacturing) ሥራ ላይ የተሰማሩትን የብድር ተጠቃሚ በማድረግ፤በማሰልጠን ተከታትሎ ለውጤት በማብቃት የጎላ ተሳትፎና አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማት እንዲሁም ለከፍተኛ ውጤት የበቁት ሴት ኢንተርፕረነሮች የሚበረታቱበትና የሚሸለሙበት አግባብ ይመቻቻል፡፡
ይህም በመሆኑ የኢንተርፕራይዞቹን ጥረትና የአስፈጻሚዎችን አስተዋጽኦ ለውጤት እንዲበቃ በሚያስችል መልኩ የተደራጀና የተቀናጀ ድጋፍና አመራር መስጠት ተገቢ በመሆኑ፣ በየደረጃው ያሉት አካላትም ለዘርፉ የሚሰጡትን ድጋፍ ለማስተባበርና ለማስፈጸም እንዲያስችል በሁለት እርከኖች የተዘጋጁ ኮሚቴዎች በዚህ መመርያ ተዋቅረዋል፡፡ ኮሚቴዎቹም
1ኛ/ ስትሪንግ ኮሚቴ (Steering Committee) የበላይ አመራሮች የሚገኙበት
2ኛ/ አስተግባሪ ኮሚቴ (Oporational Committoo) የፈጻሚ መሴቶች ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ አመራሮች አባል የሚሆኑበት ነው፡፡
ኮሚቴዎቹ በዚህ መመርያ ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ በማስፈጸም በኩል የእያንዳንዱ ኮሚቴ የስራ ድርሻና ኃላፊነት ተለይቷል፤ በተለይ የፕሮጀክቱ ተግባራት ከፌደራል እስከ አንድ ማእከል አገልግሎት ድረስ በተቀናጀና ለውጤት በሚበቃ መልኩ በመፈጸም ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ አፈጻጸሙን ለመገምገምና ክትትል ለማድረግ በሚያግዝ መልክ ሲሆን፤ መመርያው የፕሮጀክቱን የሥራ ውጤት የሚለካበት፡ እንዲሁም እገዛ የሚደርግበትና አመራርና አቅጣጫ የሚሰጥበት ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡
በተጨማሪም በሥራ ላይ ላሉት የፕሮጀክቱ ሠራተኞችና ድጋፍ ሰጪ አካላት የማበረታቻ ሥርዓት በዓይነትና በመጠን እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ በተለይም ፕሮጀክቱ የታለመለትን ግብ ከማሟላት በሻገር ለሌሎች ፕሮጀከቶችና ፕሮግራሞች አርአያ የሚሆንበት፤ ተሞክሮ የሚያካፍል እንዲሆንና ፕሮጀክቱን በማስፋት ለመላው የሀገሪቱ ኢንተርፕሪነር ሴቶች ተደራሽ ለማድረግ እንዲያግዝ በሚረዳ መልኩ ለመምራት እንዲያስችል ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡