የመመሪያ መለያ: 845/2014
ቀን: ሰኔ 1፥ 2007 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዱር እንስሳት ፊልም ቀረፃ (መመሪያ ቁጥር 845/2014)

የዱር እንስሳትና በመኖሪያ አካባቢያቸው ላይ የሚደረግ የፊልም ቀረፃ የዱር እንስሳቱን አደጋ ላይ በማይጥልና ህጋዊ በሆነ መንገድ እነዲከናወን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የዱር እንስሳት ኢ-ፍጆታዊ የአጠቃቀም ስልት አማካይነት ከዱር እንስሳት ሃብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማጎልበት ለሀገሪቱ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በዱር እንስሳት ፊልም ቀረፃ የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችን በማስወገድ ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ቀደም ሲል የወጡትን የዱር እንስሳት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 541/1999 እና የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 163/2001 ማስፈጸሚያ መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፤

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 541/1999 አንቀጽ 17 (2) በተደነገገው መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን

Ethiopian Wildlife Conservation Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration