የዱር እንስሳት ሃብት ባልተቀናጀና አግባብነት በሌለው አጠቃቀም ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነና ለአደጋ ተጋላጭነቱ እየጨመረ በመምጣቱ፤
በዱር እንስሳትና በዱር እንስሳት ውጤት ላይ የሚደረገው የንግድ የዱር እንስሳቱን አደጋ ላይ የማይጥልና ህጋዊ በሆነ መንገድ እነዲከናወን ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የዱር እንስሳት በፍጆታዊ የአጠቃቀም ስልት አማካይነት ከዱር እንስሳት ሃብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማጎልበት ለሀገሪቱ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በዱር እንስሳት የታክሲደርሚ ንግድ ሥራ ላይ የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችን በማስወገድ ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 31 የተሠጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት ይህንን መመሪያ አወጥቷል፡፡