ዌብ ፖርታል ዌብሳይት ሲሆን ተጠቃሚ በአንድ አድራሻ በመግባት የተለያዩ መረጃዎችን በአንድ ቦታ /መስኮት/ ማግኘትና መጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የሚቀመጡ መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በቀላሉ ለማደራጀት የሚያስችል ሲስተም ሲሆን ዌብ ፖርታል የተሰያዩ ኃሳፊነትና ፈቃድ የሚሰጣቸው አካሳት አስፈላጊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በኢንተርኔት ለውስጥ ተጠቃሚዎች /በኢንትራኔት/ አማካኝነት መረጃን በቀላሉ የሚያገኙበትና የሚለዋወጡበት ወቅታዊ የሆነ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ የሚገለገሉበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ከዚህ በመነሳት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በዘርፉ በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮዎችን፤ ከ70 በላይ ከተሞችንና የከተማ አስተዳደሮችን፤ አራት ተጠሪ ተቋማትንና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአስራ ሁለት ቢሮዎችን መረጃ በአንድ አድራሻ ቀተዶራጅቶ እርስ በርሳቸው ሪፖርቶች፣ መረጃዎችን የቅሬታ ማቅረቢያና ሌሎችንም አገልግሎቶችን የያዘና በየራሳቸው መረጃዎችን አጠናቅረው ለተጠቃሚው ህብረተሰብ መረጃን ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ ሰማሠራጨትና ለመጠቀም ደረጃውን የጠበቀ በኢንተርኔት፣ በወረዳኔትና በኢንትራኔት መጎበኘት የሚቻል ዌብ ፖርታልና ዌብሳይት ሠርቶ ተግባራዊ አድረጓል፡፡
ዌብ ፖርታሉ በዘርፉ ሁሱም አካላት የየራሳቸው ድረ-ገፆች ኖሯቸው መረጃ ማስገባት፣ ማስተካከል፣ ማስተዳደርና ማደራጀት የሚችሉ ሲሆን የራሳቸው ገጽ ከኃላፊነትና ተጠያቂነት ጋር በባለቤትነት መንፈስ አንዲሠሩበት የይለፍ ቃል (Password)፤የመለያ ስም (User Name) አጠቃቀምና ሌሎችም ተያያዥ የደኅንነት ጉዳዮችን በመመሪያ መደገፍ አስፈላጊ ከመሆነ- በተጨማሪ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፈጣን የለውጥ ሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ይህን ለውጥ ዘመን ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃን በውስጥ ኢንትራኔትና በወረዳኔት ለውጭ በኢንተራኔት አማካኝነት በቀላሉ ለመሰዋወጥና አገልግሎቱንም ለተጠቃሚው ተደራሽ ለማድረግ የዌብ ፖርታል አስተዳደርና አጠቃቀም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡