የመመሪያ መለያ: 9/2012
ቀን: ነሐሴ 4፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የውሃ ቆጣሪ ንባብ ሥራ የአሠራር መመሪያ ቁጥር 9/2012

ባለስልጣኑ ለእያንዳንዱ የውሃ አገልግሎት ደንበኛ በውል የውሃ ቆጣሪ በመግጠም የደንበኞችን አጠቃቀም በየወሩ በሚወሰድ ንባብ እና በባለስልጣኑ የውሃ ሽያጭ ታሪፍ መሠረት የየወሩን የአገልግሎት ክፍያ የሚሰበስብ ሲሆን ይህም ባለስልጣኑ በአዋጅ ተፈቅዶለት ከሚሰበስባቸው ገቢዎች ዋነኛው እና በቀጥታ በውሃ ቆጣሪ ንባብ ጥራት ላይ መሠረት ያደረገ በመሆኑ፡፡

የውሃ ቆጣሪ ንባብ ላይ የሚከሰቱት ችግሮች ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን ከፍተኛ የውሃ ዋጋ እንዳይጠየቁ የማድረግ፣ የደንበኞች ቆጣሪ በወቅቱ ሳይነበብ በመቅረቱ ለተራዘመ ጊዜ የቆጣሪ ግብር ብቻ የሚጠየቁ እና ደንበኞች አጠቃቀም ከፍተኛ የታሪፍ ምድብ ውስጥ መግባት አለግባብ ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉ የማድረጉ፣ አዲስ የውሃ ቆጣሪ የተገጠመላቸውን ደንበኞች የመጀመሪያ ንባብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አለመነበቡ ደንበኞች የፍጆታ ሂሳባቸውን በወቅቱ ለመክፈል እንዲይችሉ በማድረጉ እና ደንበኞች በየወሩ አንባቢው ያነበበውን ንባብ በንባብ ካርድ ላይ ባለመጻፉ ትክክለኛ ንባብ ስለመወሰዱ ለማረጋገጥ ባለመቻላቸው በቆጣሪ ንባብ ስራ ላይ የግለፅነትና ተጠያቂነት እንዳይኖር እንቅፋት በመፍጠሩ ባለስልጣኑ ይህን ዋነኛ ገቢውን በወቅቱ እንዳይሰበሰብ ከማድረጉም በላይ በደንበኞች ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረ በመሆኑ፡፡

ይህንን የውሃ ቆጣሪ ንባብ ተግባር ችግር በመቅረፍ የንባብ ስራውን በጥራትና ተጠያቂነት በሰፈነበት ሁኔታ ለማከናወን የሚረዳ እና የደንበኞች የውሃ አገልግሎት ሂሳብ ክፍያን ከቅሬታ የፀዳ እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ ባረጋገጠ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችል እና ባለስልጣኑ ዋነኛ ገቢውን በጥራት እና በብቃት መሰብሰብ የሚያስችል አሠራር መኖር ያለበት መሆኑ በመታመኑ፡፡

በአዱስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

Addis Ababa Water and Sewerage Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration