የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚያከናወነውን የምግብና የጤና ነክ ምርትና ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ቁጥጥር ስራን ማጠናከር የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ህገ-ወጥ ምርት፣ ደህንነቱና ጥራቱ ያልተጠበቀ ምርት እና ሕግን ያልተከተለ አገልግሎት አሰጣጥ ምክንያት ለማኅበረሰብ ጤና ስጋት አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ፤
በፌደራል ደረጃ የወጣውን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር60/2006 በዝርዝር ለማስፈጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2012 አንቀጽ 44 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 60/2006 አንቀጽ 97 መሠረት ባለስልጣኑ ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡