ባልተጠና እና ባልተቀናጀ መንገድ የሚወሰኑ የጎብኚዎች የክፍያ ትመናዎች በቱሪዝም አገልግሎት አሠጣጥ ላይ ክፍተት በመፍጠር የሀገሪቱ ገፅታ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያስከተለ በመሆኑ፤
ተገቢው የጎብኚዎች የክፍያ ተመን ሥርዓት ባለመዘርጋቱ ሀገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ ጥቅሞች እንድታጣ በማድረጉ፤
ወጥነት በሌለው አሠራር የሚወሰኑ የጎብኚዎች የክፍያ ተመኖች በጎብኚዎች ፍሰት፣ የቆይታ ጊዜ እና የእርካታ ደረጃ ላይ አሉታዊ ተፀዕኖዎች እያስከተለ በመሆኑ፤
የጎብኚዎች የክፍያ ተመን አወጣጥ ወጥ፣ ግልፅና ፍትሐዊ በሆነ የአሠራር ስረዓት በመምራት የአገር ውስጥና የዓለም ዓቀፍ ቱሪዝምን ለማስፋፋት አመቺ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር 9 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡