በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ሥርአቱን ፍትሃዊ፣ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ነጋዴዎችና ሽማቹ ህብረተሰብ ከንግድ ሥርአቱ የሚጠብቀውን ትክክለኛ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ እና ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን መግታት በማስፈለጉ፤
በሁሉም ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች ሕግን መሠረት በማድረግ ወጥነት ያለው ግልጽ፣ ተጠያቂነት፣ ያለበት የክትትልና የቁጥጥር የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በከተማ ውስጥ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 2 ፊደል (ሠ) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡