የመመሪያ መለያ: 14/2012
ቀን: ነሀሴ 7፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የእንስሳት መድኃኒትና ሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ችርቻሮ ንግድ ተቋም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 14/2012

የተሟላ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ፈዋሽነታቸው፣ ደህንነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶች በማያቋርጥ ሁኔታ መገኘትና በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ወሳኝነት አለው:: መንግሥት በሽታን ለመመርመር፣ ለመከላከልና ለማከም የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች በአግባቡ እንዲቀርቡ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የመቆጣጠር ግዴታ አለበት፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ የእንስሳት መድኃኒቶች ከእንስሳት ጤንነትና ምርታማነት ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ፣ በተፈጥሮአቸው የመርዛማነት ባሕርይ ያላቸውና ከጥሬ ዕቃዎች ዝግጅት ጀምሮ በምርት፣ በክምችት አያያዝ፣ በማከፋፈልና በችርቻሮ ሂደት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ካልተደረገበት የጥራት ደረጃቸው፣ የፈዋሽነታቸውና ደህንነታቸው ባህርይን ሊያጡ ወይም ሊለወጡ ስለሚችሉ ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም እስከ ማሳጣት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡

ስለሆነም የእንስሳት መድኃኒት ዕደላ መካሄድ ያለበት በሙያው ጠለቅ ያለ ዕውቀትና አግባብ ባለው ባለሙያ ነዉ:: በተጨማሪም ጥራታቸው፣ ፈዋሽነታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ የእንስሳት መድኃኒቶች ለተገልጋዩ ለማዳረስ ለክምችት፣ አያያዝና ዕደላ አመቺ የሆነና የተሟላ ተቋም መኖር አለበት፡፡

በመሆኑም የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 728/2004 አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት የእንስሳት መድኃኒቶች ዕደላ ተግባር መመዘኛዎችና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት በተገቢው መንገድ እንዲከናወን ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የእንስሳት መድኃኒትና የእንስሳት መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን

Veterinary Drug and Animal Feed Administration and Control Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration