የመመሪያ መለያ: 743/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የተጠቃሚዎች የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ ቁጥር 743/2013

በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙና ለምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንዲቻል የኢፌዲሪ መንግሥት የከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂና ፕሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋነኝነት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ እና ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማለትም እጅግ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ሴተኛ አዳሪዎችን፣ መሥራት እየቻለ ወደ ስራ ያልገቡ ስራ ፈላጊ ዜጎችን አካል ጉዳተኞችን የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎች፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያን እና ህጻናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ::

ይህ ፕሮጀክት በከተሞች በከፋ ድህነት ውስጥ ከሚገኙ በርካታ ዜጎች ህይወት መለወጥ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንደመሆኑ እና ከፍተኛ የሆነ ሀብት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ባዘለ ሁኔታ ሊተገበር እንደሚገባው አያጠያይቅም፡፡ ፕሮጀክቱን ውጤታማ ለማድረግ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች መካከልም ተጠቃሚዎችን በቤተሰብ ደረጃ ፍትሃዊና አሳታፊ በሆነ መንገድ መለየት ዋነኛው ሲሆን በተያያዘም በተጠቃሚዎች ልየታ እና በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ትግበራ ሂደት ሊከሰቱ የሚችሉ ቅሬታዎችን በአግባቡ ተቀብሎ መፍታት ይገኝበታል፡፡

በመሆኑም፡-

ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ምልመላ ጀምሮ በየደረጃው በሚኖረው የትግበራ ሂደት ሊከሰት የሚችለውን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል የቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ የአሠራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

ፕሮጀክቱን ከኪራይ ሰብሳቢነት በጸዳ እና ግልጽነትና ተጠያቂነት ባሰፈነ መልኩ በመተግር የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 374/2008 አንቀጽ 14 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የተጠቃሚዎች የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ አውጥቷል ፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration