የመመሪያ መለያ: 742/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የከተሞች ምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተጠቃሚዎች መመልመያ መመሪያ ቁጥር 742/2013

በከተሞች የሚገኘውን የስራ አጥነትና ድህነት ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ እና ወደ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ ሀገራችን ራዕይ ሰንቃ ጉዞ ጀምራለች፡፡ ይህንኑ ለማስፈጸም በርካታ የልማት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው ስራ ላይ የዋሉ ሲሆን በከተሞች እየተተገበረ ያለው የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የቤቶች ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ የተመዘገቡት ውጤቶች አመርቂ ናቸው፡፡ በከተሞች እየተከናወነ ካለው የስራ ዕድል ፈጠራ ጎን ለጎን ከድህነት ወለል በታች ላሉ ዜጎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መንግሥት የከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂና ፕሮግራም ቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በዋናነኝነት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን በተለይም በከተሞች አካባቢ የሚታዩ በድህነት ውስጥ የሚገኙ እና ለተለያዩ የማኅበራዊ ችግርና ጠንቅ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለመግባት ከሚሰሩት ዋነኛ ስራዎች መካከል ተጠቃሚዎችን በቤተሰብ ደረጃ መለየት አንዱ ሲሆን የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን ከኪራይ ሰብሳቢነት በጸዳ እና ግልጽነትና ተጠያቂነት ባሰፈነ መልኩ ለመለየት የቤተሰብ ተጠቃሚዎች የመመልመያ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ በፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ መቋቋሚያ ደንብ 374/2008 አንቀጽ 14 መሠረት ሚንስቴሩ ደንቡን ለማስፈጸም የሚያስችል በደንብ ላይ በተቀመጠው መሠረት ይህ የተጠቃሚዎች መመልመያ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration