በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ የገቢ ግብር አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 286/1994) በአንቀጽ 29 በተመለከተው መሠረት ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከለ የሚደረጉ ግብይቶች የገበያ ዋጋ መርህን ተከትለው መከናወን ስላለባቸው፣
ዓለም አቀፍ መልካም ተሞክሮዎችን (በተለይም ደግሞ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር ድርጅት የማስተላለፊያ ዋጋ መመሪያዎችን) መሠረት ያደረገና የገበያ ዋጋ መርህን ሥራ ላይ ለማዋል የሚጠቅም፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ በማስተላለፊያ ዋጋ የሚደረግ ግብይትን ለመከላከለ የሚያስችል አሠራር መዘርጋት በማስፈለጉ፣
በገቢ ግብር አዋጅ አንቀጽ 29(1) ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ መ/ቤቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡