የመመሪያ መለያ: 122/2013
ቀን: ኅዳር 17፥ 2001 ዓ.ም.
Language: Amharic

የክልል መንግስታትና ከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቅድመ ታክስ ክፍያ እና ሌሎች የጋራ ገቢዎች ስለሚተላለፉበት አሰራር የወጣ መመሪያ ቁጥር 122/2013

ከክልል መንግስታትና ከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዮች የሚሰበሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ገቢ በመሆኑ በወጪ አሸፋፈናቸው ላይ ተጽእኖ በማያስከትል ሁኔታ በወቅቱ መተላለፍ ስለሚኖርበት፣

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 52 እና አንቀጽ 53 አማካይነት በሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው ከተከፋይ ሂሣቦች ላይ በቅድሚያ ተቀናሽ የሚደረገው የቅድመ-ታክስ ክፍያ ገቢ ባለቤት ለሆኑት ገቢ ሰብሳቢ አካላት የሚተላለፍበትን ሥርዓት በወጥነት መዘርጋት በማስፈለጉ፣

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት የጋራ ገቢዎች ስለሚከፋፈሉበት ቀመር ላስተላለፈው መመሪያ ተግባራዊነት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተሰጠውን ውክልና ተፈፃሚ በማድረግ የክልል መንግሥታትና የከተማ አስተዳደሮች ከጋራ ገቢ ድርሻቸውን በወቅቱ እንዲያገኙ ለማስቻል፣

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በየሚኒስትሮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 አንቀጽ 27 እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 39 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የአፈፃፀም መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

Ethiopian Revenue and Customs Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration