የንግድ ትርዒትና ባዛር አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የንግድና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት፣ የንግድ ውድድር እየጨመረ በመምጣቱ፤ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየወጣባቸው ወደ አገርውስጥ የሚገቡትን ምርቶች በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ እንዲቻል፤ በአምራቾች፣ አገልግሎት ሰጭዎችና ተጠቃሚዎች መካከል በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ የተመሠረተ የንግድ ልውውጥ ጤናማ የንግድ ግንኙነት በአግባቡ ለመምራት ወቅቱ በፈጠራቸው ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተመረቱትን ምርቶች ለማስተዋወቅና የሸማቹን ፍላጎትና የመግዛት አቅም ባገናዘበ መልኩ የንግድ ሥርዓቱን በሕግ አግባብ መምራት በከተማችን የንግድ ትርዒትና ባዛር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ይታወቃል፡፡
በዚህ መሠረት በንግድ ትርዒትና ባዛር ፈቃድ አሰጣጥና አፈጻጸም ዙሪያ እየታዩ ያሉትን ችግሮች ለማስወገድ እና በተገቢው መንገድ ለመምራት እንዲቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 16 (2) (ሠ) እና 31(2) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡