የመመሪያ መለያ: 808/2013
ቀን: ነሐሴ 14፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የጎብኚዎች ደህንነት መመሪያ ቁጥር 808/2013

በዓለም አቀፍ ደረጃ ባልተለመደ ሁኔታ በተቀሰቀሰው የበሽታ ወረርሽኝ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ የደቀነው አደጋ በተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተለ በመሆኑ፤

በኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት መንግስታት የወሰዱትን ፈጣንና ጠንካራ እርምጃዎች ተከትሎ ገደብ ተጥሎባቸው የነበሩ የጉብኝት እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ እየላሉና በበርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን በድጋሚ እየተጀመሩ በመሆኑ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ በማስተዳደር ለማስጀመር እንዲያስችል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ደህንነቱ የተጠበቀ የጉብኝት ፕሮቶኮል እና የአሠራር ስርዓት መቀበል አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤

የጎብኚዎችን እምነት በድጋሚ ለመገንባት እና የቱሪዝም ዘርፍ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የተሰማሩ ሰራተኞች የጤና ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ግልፅ፣ ወጥ እና ፍትሐዊ የአሠራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈልጉ፤

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 30 የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Ministry of Culture and Tourism

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration