የመመሪያ መለያ: 682/2013
ቀን: ህዳር 1፥ 2009 ዓ.ም.
Language: Amharic

የተሽከርካሪ ማስቆሚያ ታፔላ የአጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 682/2013

በአዋጅ ቁጥር 4597 አንቀጽ 7 /2 / ኸ/ መሠረት ባለሥልጣኑ መ ቤት በአውራ ጎዳናዎች ላይ የመንገድ ትራንስፖርት አዋጆች ፤ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን የመከታተል ሥልጣን በተሰጠው መሠረት የተሸከርካሪ ማስቆሚያ ታፔላዎች በሠሌዳና ምልክቶች ምርትና ስርጭት ዳይክቶሬት እየተመረተ ለትራንስፖርት መ/ቤት፤ ለክልል ትራንስፖርት ቢሮዎችና ለትራንስፖርት ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ሲሰራጭ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁንና ከዚህ በፊት የተመረተው የተሽከርካሪ ማስቆሚያ ታፔላ በሕጋዊና በሕወጥ መንገድ በተለያዩ ግለሰቦች እጅ በመግባቱ ለሕገወጥ ስራ እየተጠቀሙበት ስለሆነ ይህን ለመለየትና ለማሰባሰብ አስቸጋሪ ስለሚያድገው ከዚህ በፊት የነበረው አገልግሎት ላይ እንዳይውል ማስወገዱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በዚህ መሠረት እስከ አሁን ሥራ ላይ የነበረው የተሸከርካሪ ማስቆሚያ ታፔላ መደቡ ነጭ ክቡ ቀይ የሆነውን በመቀየር እንደ አደረጃጀቱ ዓይነት በተለያዩ የቀለም ህብር በመተካት አመራረቱና ስርጭቱ እንዲሁም አጠቃቀሙን በመመሪያ ሥርዓት ማስያዙ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Ministry of Transport and Logistics

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration